CONCENTRIC MEDIA

The Work of DOROTHY FADIMAN

Home >> Films

የተስፋ ዘርተከታታይ የኢትዮጵያ ፊልሞች

Photo Credit: Sisse Brimberg SEEDS of HOPE kids group shot

Website: SeedsofHopeFilms.org

የተስፋ የአምስት ዘጋቢ ፊልሞች ስብስብ ሲሆንፊልሞቹም ግለሰቦች እና ድርጅቶች| በኤድስ ዙሪያ ያለውን ዝምታ ለመስበርመገለልን ለማስወገድእንዲሁም የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረቶች ያሳያሉ፡፡ በፊልሞቹ አማካይነትኤድስን በመከላከል ተግባር ላይ የተሰማሩ ልበ ቀናዎችን| የቤተሰብ አባላትንለሰብአዊነት ያደሩ ቡድኖችንእንዲሁም እንክብካቤ የሚያደርጉ የጤና ባለሙያዎችን ደፋ ቀና ሲሉ እናገኛቸዋለን፡፡ አንዳንዶቹ| የድጋፍ አገልግሎት በማበርከት ስራ ላይ የተሰማሩ ሲሆን ሌሎቹ ሁሉም ስለኤድስ ያለው አጠቃላ እውቀት ይበልጥ እንዲዳብር ዘወትር የሚተጉ ናቸው፡፡ ሁሉም ዘጋቢ ፊልሞችየተስፋን እና| ሰዎችን የማብቃት መልእክት በውስጣቸው ይዘዋል፡፡ ተከታታይ ፊልሞቹኤድስ በአፍሪካ ከሚገለፅበት የተለመደ መንገድ ወጣ በማለትኤች አይቪ በደማቸው ያለባቸው ግለሰቦች በቀን ተቀን ህይወታቸው የሚያሳልፏቸውን ልዩ አጋጣሚዎችን እና ኩነቶችን ይዘግባሉ፡፡ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት በህይወት ባለ የቤተሰብ አባል ወይንም ህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ ህይወትን ሲገፉ ፊልሞቹ ያሳያሉ፡፡ወጣቶችድራማና | ስነ ግጥምን የመሳሰሉ ስልቶችን በመጠቀም እኩዮቻቸውን ሲያስተምሩበወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶች ኮንዶምን በተመለከተ እርስ በርስ ሲማማሩ እና ደንበኞቻቸውን ሲያስተምሩእንዲሁም የድጋፍ አገልግሎት ባለሙያዎች ከበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ተጣምረው ሲሰሩ ፊልሞቹ ያሳያሉ፡፡ እነዚህን ግላዊ የሰዎች ታሪክ በማቅረብየዘጋቢ ፊልሞቹ ባለቤቶችኢትዮጵያዊያንን ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሀገር ያሉ ሰዎቸን ጭምር ኤድስን በመዋጋት ስራ ላይ እንዲተጉ ለማነሳሳት ይረዳሉ ብለው ያምናሉ፡፡ ተከታታይ ፊልሞቹሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ላለባቸው ግለሰቦች የሚሰጡትን አገልግሎት በበለጠ ፍቅር እንዲሰሩት የማድረግ አላማም አላቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪከኤድስ ጋር በተያያዘማህበራዊ ፍትህን እና ሰብአዊ ክብርን ለማስገኘት ደፋ ቀና የሚሉ ሰዎችን ሁሉ አይዟችሁ ማለት እንፈልጋለን፡፡ የእንግሊዘኛ ትርጉም ያላቸውን እነዚህን በአማርኛ የተሰሩ ፊልሞች በአማርኛ ትረካ ብቻ ማግኘትም ይቻላል፡፡

የተከታታይ ፊልሞቹ ግብ እንዲሁም ተስፋ

የኛ የፊልሙ ባለቤቶች ዋና አላማኤድስ | በአፍሪካ ከሚገለጽበት መንገድ ወጣ ብለንለተመልካቾቻችን አዲስ እይታ ማቅረብ ነው፡፡ተከታታይ ፊልሞቹኤድስ ለወትሮው ከሚገለፅበት የተለመደ መንገድ ወጣ በማለትኤች አይቪ በደማቸው ያለባቸው ግለሰቦች በቀን ተቀን ህይወታቸው የሚያሳልፏቸውን ልዩ አጋጣሚዎችን እና ኩነቶችን| በመዘገብ| ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናት በጎረቤት እርዳታ ሲያድጉ በማሳየት| ወጣቶችድራማና| ስነ ግጥምን የመሳሰሉ ስልቶችን በመጠቀም እኩዮቻቸውን ሲያስተምሩ በማሳየትበወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶች ኮንዶምን በተመለከተ| ደንበኞቻቸውን ሲያስተምሩ በማሳየትኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን በተቀረው አለም የሚኖሩ ሰዎችም| ኤች አይኤድስን በመከላከል ስራ ላይ እንዲሰማሩማህበራዊ ፍትህን እና ሰብአዊ ክብርን ለማምጣት በሚደረገው ትግል ላይ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ማነሳሳት ይቻላል ብለን እናምናለን፡፡ አምስቱም ዘጋቢ ፊልሞች አንድ ላይ ሆነው የተዘጋጁበት ቅጂ ከሁለት መቶ ለሚበልጡ ኢትዮጵያውያን የማህበረሰብ ቡድኖች እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ድጅቶች ተሰራጭተዋል፡፡ እነዚህም ድርጅቶች ተከታታይ ፊልሞቹን ስለ ኤድስ ያለውን የማህበረሰቡን እውቀት ለማሳደግ እና | በሽታውን ለመከላከል እና ድጋፍ ለመስጠት ህዝቡን| እያንቀሳቀሱበት ይገኛሉ፡፡

በዲቪዲ መልክ የተዘጋጀው የተከታታይ ፊልሞቹ ቅጂ ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ፣ እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ ኤች አይ ቪን በመከላከል ስራ ላይ ለተሰማሩ የማህበረሰብ ቡድኖች ተሰራጭቶ ፣ ከፍተኛ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል ፡፡   የተለያዩ ምርምሮችአፍሪካ አሜሪካውያን ለቫይረሱ ያላቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ እንደሆነ ቢያሳዩምእነዚህን ወገኖች ለመድረስ የሚደረግ ጥረት ግን እምብዛም አይታይም፡፡ ኢትዮጵያውያን ማህበራትን ለመደገፍ የሚደረጉ ጥረቶችለህዝብ የሚተላለፉ የቴሌቪዥን ስርጭቶች| እንዲሁም የጤና ግልጋሎት የሚሰጡ ልዩ ልዩ ተቋሞችእነዚህ ተከታታይ ፊልሞች አስተማሪ እና በጎ ስራን ለማስተዋወቅ ትልቅ መሳሪያዎች እንደሆኑ ያምናሉ፡፡